Fana: At a Speed of Life!

የታይዋን ምክትል ፕሬዚዳንት አሜሪካ መግባት ቻይናን አስቆጣ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የታይዋን ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሌይ አሜሪካ ኒውዮርክ መግባት ቻይናን ክፉኛ ማስቆጣቱ ተሰምቷል፡፡

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ÷ ቤጂንግ የታይዋን ምክትል ፕሬዚዳንት ወደ ፓራጓይ ለስራ ሲያቀኑ አሜሪካ ማረፋቸውን በቀላሉ አታየውም፡፡

ቻይና÷በአሜሪካ እና ታይዋን መካከል የሚደረግን ማንኛውንም አይነት ይፋዊ ግንኙነት አጥብቃ እንደምትቃወም መግለጫው አመላክቷል፡፡

ዊሊያም ሌይ በአሜረካ ያደረጉት ቆይታም የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚዳፈር ነው ሲል ሚኒስቴሩ አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

ድርጊቱን ተከትሎም ቻይና በታይዋንላይ ጠንካራ እርምጃዎችን እንደምትወስድ ማስጠንቀቋን ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡

ቻይና ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለች መሆኑን ያነሳው መግለጫው÷በሀገሪቱ ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ላይ የሚቃጡ ድርጊቶችን እንደማትታገስ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.