Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የጤና ማዕከል የቦታ ጥያቄ ላይ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 12 ሆስፒታሎች በጋራ የጤና መንደር ለመገንባት ባቀረቡት የመሬት ጥያቄ ላይ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የአስተዳደሩ ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው 3ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2015 ዓመታዊ ስራ አፈፃፀሙን ገምግሟል፡፡

ካቢኔው ለመጀመሪያ ጊዜ ከተለያዩ ፓርቲ የተውጣጡ አባላቱን በማሳተፍ የጋራ ውሳኔ ማስተላለፍ ላይ የሄደበት ርቀትና እየገነባ ያለው የዲሞክራሲ ባህል በጥንካሬ ተነስቷል፡፡

የሕብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስና ለችግሮቹም ተመጣጣኝ መፍትሔ ለመስጠት የሄደበት የጋራ አመራር አሰጣጥና የማስፈፀም አቅም አበረታች መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የአሰራር ስርዓትንና አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሻሽሉ እና የከተማ ስራን የሚያሳልጡ፣ በከፍተኛ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ 181 ስትራቴጂክ የሆኑ ችግር ፈቺ ውሳኔዎችን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ካቢኔው ማሳለፉ ተጠቅሷል፡፡

ከውሳኔዎቹ 145ቱ በተሟላ ሁኔታ መፈፀማቸው የተገለጸ ሲሆን ይህም በስኬት ተነስቷል በግምገማው፡፡

ከተላለፉ ውሳኔዎችም 24 የሕግ ሰነዶችን ማፅደቅ መሆኑን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በከተማዋ የመሬት አቅርቦት፣ ለተለያዩ የከተማዋ መሰረታዊ ፍላጎት የበጀት ድጎማ፣ የስራ እድል መፍጠር፣ የኑሮ ጫናን የሚያቃልሉ በየወቅቱ ለሚነሱ ማህበራዊ ጥያቄዎች ልዩ ውሳኔ እንደ ባህሪያቸው መደረጋቸው በውጠየታማ ነት ቀርበዋል፡፡

የካቢኔውን ውሳኔዎች በሚፈለገው ፍጥነት አለመተግበር፣ መረጃ ለሕብረተሰቡ በወቅቱ አለማድረስ የሚሉትና ሌሎችም በክፍተት ተነስተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.