Fana: At a Speed of Life!

የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአፋር ክልል አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር እና በስሩ የሚገኙ ተጠሪ ተቋማት በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ ያህሌ ቀበሌ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተገኝተዋል፡፡

የሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችም በዱብቲ ወረዳ ያህሌ ቀበሌ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሐ -ግብር መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አቶ አህመድ ሽዴ በአፋር ክልል በሚኖራቸው ቆይታ በዱብቲ ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቤት ማደስ መርሐ ግብርን ያስጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.