Fana: At a Speed of Life!

በካይዘን ልህቀት ማዕከል በተሰሩ ስራዎች ከ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ብክነት መቀነስ መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በካይዘን ልህቀት ማዕከል በተሰሩ የክትትልና ድጋፍ ስራዎች ከ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ብክነት መቀነስ መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።

ሚኒስትሩ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማሳን እና ሌሎች የመንግስትና የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ አመራሮች ጋር በመሆን አዲሱን የካይዘን ለህቀት ማዕከል ጎብኝተዋል፡፡

በዚህ ወቅት አዲሱ የከይዘን ልህቀት ማዕከል በዓመት 50 ሺህ ሰልጣኞችን ማሰልጠን የሚችል አቅም እንዳለው ገልጸዋል።

እስከ አሁን በከይዘን ማማከርና ድጋፍ በተሰሩ ስራዎች ከ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ብክነት መቀነስ የሚያስችል ውጤት ማምጣት እንደተቻለ አስረድተዋል፡፡

የጃፓን የማምረት ፍልስፍና በአፍሪካ ውስጥ ውጤታማ ከሆኑባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ተጠቃሽ መሆኗን ያነሱት ሚኒስትሩ፥ በኢትዮጵያ 1 ሺህ 500 ለሚሆኑ አምራች ኢንዱስትሪዎች የካይዘን ድጋፍ በማድረግ ብክነትን በመቀነስ ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉንም ነው የተናገሩት።

የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማሳን በበኩላቸው በልህቀት ማዕከሉ የተሰሩ ስራዎችን አድንቀው፥ በቀጣይ ጃፓን የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

በጃፓን መንግስት ድጋፍ የተገነባው ዘመናዊ የካይዘን ልህቀት ማዕከል በመጪው ጥቅምት ወር ተመርቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.