Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ብቻ 17 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ1 ሺህ 382 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 17 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 162 ደርሷል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥ ሰባቱ ከጂቡቲ የተመለሱና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆኑ፥ ስድስቱ ደግሞ ከሶማሊያ የተመለሱና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

አራቱ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ፥ ሁሉም የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።

ከእነዚህ ውስጥ የ27 አመቱ ወጣት የስራው ባህሪ ተጋላጭነት ያለው ሲሆን፥ የ28 አመቷ ወጣት እና የ53 አመቷ ሴት ደግሞ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው።

የአፋር ክልል ነዋሪ የሆነውና አዲስ አበባ ከተማ የተገኘው የ39 አመቱ ኢትዮጵያዊ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ንክኪ እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 63 ሲሆኑ፥ 93 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል ተብሏል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.