Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከቱሪዝም ዘርፍ ከ103 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ከጎበኙ 40 ሺህ 600 ጎብኚዎች ከ103 ሚሊየን 199 ሺህ ብር በላይ ቀጥተኛ ያልሆነ ገቢ ተገኘ፡፡

የቱሪዝም ዘርፉ አፈጻጸም ከአለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 18 በመቶ ብልጫ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

በክልሉ ከአለፈው ዓመት በተሻለ ሁኔታ በሦስቱም ዞኖች አንጻራዊ ሰላም መኖሩ እና መዳረሻዎችን በማልማት ለጎብኚዎች ክፍት ማድረግ መቻሉ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ምክንያት እንደሆነ ተጠቅሷል።

የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር ታምራት ሙሊሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ 40 ሺህ የሀገር ውስጥ እና 600 የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ክልሉን ጎብኝተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.