Fana: At a Speed of Life!

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ በሴቶች የዓለም ዋንጫ አሜሪካን ወክላለች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማ በሴቶች የዓለም ዋንጫ በአሜሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ስብስስብ ውስጥ ድንቅ ብቃቷን እያሳየች ትገኛለች፡፡

የተካላካይ ክፍል ተጫዋቿ በፈረንጀቹ 2020 የአሜሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጥሪ የደረሳት ሲሆን፥ አሜሪካ ኡዝቤኪስታንን ባሸነፈችበት ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ 90 ደቂቃ ተሰልፋ መጫዎት ችላለች፡፡

በሰሜን አሜሪካ የሴቶች ሻምፒዮና ውድድር አራት ጊዜ ተሰልፋ መጫወት የቻለችው ናኦሚ የአሜሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለ2023 የፊፋ የሴቶች የዓለም ዋንጫ እና ለ2024 የበጋ ኦሊምፒክ እንዲያልፍ አስተዋፅዖ አድርጋለች፡፡

ናኦሚ በኒውዝላንድ እና አውስትራሊያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው 9ኛው የሴቶች የዓለም ዋንጫ በአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ስብስስብ ውስጥ በመካተት ድንቅ ብቃቷን እያሳየች ትገኛለች፡፡

ናኦሚ በ2019 የኮሌጅ ቡድኗ ስታንፎርድ ዋንጫ እንዲያነሳ አስተዋፅዖ ያደረገች ሲሆን በምርጥ 12 የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾች ስብስብ ውስጥም መካተት መቻሏን የአሜሪካ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

በ2020 የአሜሪካ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድንን በአምበልነት መምራት የቻለችው ኖኦሚ በዚሁ ዓመት የአሜሪካ ምርጥ ወጣት ሴት ተጫዋች በመሆን ተመርጣለች፡፡

ናኦሚ ከኢትዮጵያ ወላጅ አባቷ አቶ ግርማ አወቀ እና ከእናቷ ወይዘሮ ሰብለ ደምሴ በፈረንጆቹ 2000 የተወለደች ሲሆን አሁን ላይ 23 አመቷ ላይ ትገኛለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.