Fana: At a Speed of Life!

ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ተሰጣት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ባስመረቀበት ወቅት ነው ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት የሰጠው፡፡

በመርሐ ግብሩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር)÷አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የሀገሯን ሙዚቃና ባህል እንዲሁም የተወለደችበትን የአገው ህዝብ ባህልና ቋንቋ ለዓለም ህዝብ በማስተዋወቋ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስቷ የክብር ዶክትሬት ሲሰጣት ታላቅ ክብር ይሰማዋል ብለዋል፡፡

ጂጂን ማክበር ጥበብን ማክበር ነው ያሉት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር)÷ጂጂን ማክበር የኢትዮጵያን ታሪክና ጀግኖችን እንዲሁም ፍቅርንና አንድነትን ማክበር ነው ብለዋል፡፡

ተቋሙ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲውን በታሪክ ሊያስታውስ የሚችል የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለድንቋ ድምጻዊትና ለጥበብ ንግስት ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) በሚሰጥበት እለት መሆኑ መርሐ ግብሩን ለየት ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በየሻምበል ምሕረት

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.