የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎችን ለማደራደር መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳንን የዕርስ በርስ ግጭት ለመፍታት ተፋላሚ ሀይሎችን ለማደራደር በነገው እለት በአዲስ አበባ በመሪዎች ደረጃ ውይይት ይካሄዳል።
በዚህ ውይይት የሚሳተፉ የተለያዩ አገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
ከመሪዎቹ መካከልም የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የጅቡቲው የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር መሀመድ አሊ ይገኙበታል።
መሪዎቹ አዲስ አበባ ሲገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል እንደተደረገላቸው ኢፕድ ዘግቧል።
ሰኔ 5፣ 2015 ዓ.ም በጂቡቲ በተደረገው የኢጋድ መደበኛ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ኢጋድ የሱዳንን ግጭት እንዲያሸማግሉ የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ጅቡቲና ደቡብ ሱዳን መሪዎች መሰየሙንም ዘገባው አስታውሷል።