Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ፀጥታ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ፀጥታ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በተገኙበት አካሂዷል፡፡

በመድረኩ ምክር ቤቱ አጠቃላይ የክልሉ ሕዝብ ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ ላይ የተዘጋጀ ሪፖርትን ገምግሟል፡፡

በተጨማሪም የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ሰላምና ፀጥታ የሚፋጠንበትን አቅጣጫና መመሪያ መስጠቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ ላይ የሶማሌ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ጠይብ አሕመድ ኑር፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አብዲ አሊ ዚያድ እና ሌሎች የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ አመራሮች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.