Fana: At a Speed of Life!

በኤሌክትሪክ አደጋ እናትና ልጅን ጨምሮ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ እና ደቡብ ክልል በኤሌክትሪክ አደጋ እናትና ልጅን ጨምሮ የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ትናንት ከቀኑ 9:10 ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አትላስ ፊትለፊት በሚገኝ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር ላይ ዕድሜው 35 ዓመት የሚገመት ግለሰብ በኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወቱ አልፏል።

አስከሬኑን ለፖሊስ ማስረከባቸውን ጠቁመው÷ በአዲስ አበባ በሁለት ወራት ውስጥ በኤሌክትሪክ አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስታውሰዋል፡፡

በሌላ በኩል በደቡብ ክልል ሀላባ ዞን አቶቴአሎ ወረዳ ጤፎ ጩፎ ቀበሌ ከኤሌክትሪክ ምሰሶ ላይ ተቆርጦ የወደቀ የኤሌክትሪክ ገመድ የእናትና ልጅን ሕይወት ቀጥፏል፡፡

በአደጋው የ23 ዓመቷ እናት ከ2 ዓመት ልጇ ጋር ሕይወታቸው ማለፉን የደቡብ ክልል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.