Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓታት ለ766 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ አራቱ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ766 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ አራቱ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ እንዳስታወቁት፥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል የ15፣ የ18 እና 25 ዓመት ታዳጊና ወጣት ሴቶች ከፑንትላንድ የተመለሱና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ናቸው ብለዋል።

አራተኛው ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ ደግሞ የ23 አመት ወጣት ሲሆን፥ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሃረርጌ ጉባ ኮሪቻ ወረዳ ነዋሪ ነው ተብሏል።

ወጣቱ ምንም አይነት የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን፥ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ስላለው ግንኙነትም ማጣራት እየተደረገ ነው።

በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 58 መድረሱን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.