በመቀሌና አክሱም ከተማ የሚገኙ የደም ባንኮች በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራ መግባታቸው ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በመቀሌና አክሱም ከተሞች የሚገኙ የደም ባንኮች በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራ መግባታቸውን የኢትዮጵያ ደምና ቲሹ ባንክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሐብታሙ ታዬ÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 43 የደም ባንኮች መካከል ሦስቱ በትግራይ ክልል እንደሚገኙ ነው የተናገሩት፡፡
የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የደም ባንኮቹ ወደ ሥራ እንዲገቡ ድጋፍ ሲደረግላቸው መቆየቱንም ተናግረዋል፡፡
በዚህም በአክሱምና መቀሌ የሚገኙ የደም ባንኮች በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራ እንዲመለሱ ተደርጓል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
እስካሁን ባለው ሂደትም የመቀሌ የደም ባንክ 8 ሺህ እንዲሁም የአክሱም የደም ባንክ 6 ሺህ ዩኒት ደም በማሰባሰብ አገልግሎቱን ተደራሽ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።