በደብረ ብርሃን 38 ቢሊየን ብር ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ 38 ቢሊየን ብር ላስመዘገቡ 260 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ገለጸ።
እነዚህ ኢንቨስትመንቶች በሙሉ አቅማቸው ወደሥራ ሲገቡ ለ22 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ የመምሪያው ኃላፊ ብርሃን ገብረሕይወት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ቀድሞ ፈቃድ ካገኙ ኢንዱስትሪዎች መካከል 49 ያህሉ ግንባታቸው መጠናቀቁንም ገልጸዋል፡፡
ከእነዚህ መካከል 24 ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በደብረ ብርሃን ከተማ ከ720 በላይ ኢንቨስትመንቶች መኖራቸውን ጠቁመው÷ ከ545 በላይ የሚሆኑት ኢንዱስትሪዎች ናቸው ብለዋል፡፡
በዘላለም ገበየሁ