በሁለተኛው ዙር ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ምክክር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛው ዙር ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ምክክር እየተካሄደ ነው።
በምክክር መድረኩ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ጨምሮ አጋሮች እና የልማት ደጋፊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተወካዮች ተገኝተዋል።
በዚህ ወቅትም የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ረቂቁን በተመለከተ ለተወካዮቹ ገለጻ አድርገዋል።
ተወካዮቹ የረቂቁን አካታችነት በጥንካሬ ያነሱ ሲሆን፥ ዘላቂነት፣ መልሶ ማገገም እና እድገት ላይ ትኩረት ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
በቀጣይ በረቂቁ ቁልፍ ጉዳዮች፣ መሻሻል በሚገባቸው ክፍሎች፣ ረቂቁን ለማስፈጸም በሚያስፈልጉ ጉዳዮች እንዲሁም ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ለመተግበር በሚያስፈልጉ ሀብቶች ላይ ውይይት ይካሄዳል ተብሏል።