Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውል የ15 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውል የ15 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

አብቁ የህዝብ ተቋም በመሆኑ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውል 15 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መኮንን የለውምወሰን ተናግረዋል።

እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የህክምና መስጫ የሚሆኑ እያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር ወራዊ ኪራይ የሚያወጡ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ 5 ህንፃዎችን ለግብረ ሀይሉ ማስረከቡን አንስተዋል።

የብድርና ቁጠባ ተቋሙም የ15 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍን ቼክ ለክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ አስረክቧል።

ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ በበኩላቸው÷ አብቁተ የህዝብ ሀብት በመሆኑ ለህብረተሰቡ ጤና በማሰብ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ሌሎች የግልና የመንግስት ድርጀቶች የአብቁተን አራያ ሊወስዱ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።

ሀብት የመሰብሰብ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ያነሱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ በላይነህ ክንዴ 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም በአቶ አበባው ደስታ አስተባባሪነት 17 ሚሊየን ብር ተሰብስቦ ድጋፍ መደረጉን አንስተዋል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.