Fana: At a Speed of Life!

በ4 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር የሚተገበር ተቋማዊ የድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገሪቱን ማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር ለማጠናከር የሚያስችል የ4 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ተቋማዊ ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል፡፡

ፕሮጀክቱ የአፍሪካ ልማት ባንክ በመደበው የገንዘብ ድጋፍ ለሚቀጠሉት ሶስት አመታት ተግባራዊ የሚደረግ ነው ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ በብሄራዊ ባንክና በሌሎች ተቋማት የሚሰሩ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ባለሙያዎችን የጥናትና ምርምር፣ የፖሊሲ ትንተና አቅም በማጎልበት ማክሮ ኢኮኖሚውን ለማጠናከር ፋይዳ እንዳለው ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፕሮጀክቱ የ10 አመቱን ብሔራዊ የልማት እቅድና የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ የባለሙያዎችን የጥናትና ምርምር እንዲሁም የፖሊሲ ትንተና አቅም በማጎልበት አስተዋጽኦ አለውም ነው የተባለው፡፡

በተጨማሪም ÷ለማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት ምክንያት የሚሆኑትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ ለግሉ ዘርፍ የሚቀርብ የፋናንስ እጥረት፣ እየጨመረ ለመጣው የመንግስት እዳና ለሌሎች መዋቅራዊ ችግሮች ወቅታዊ መፍትሄ ለማፈላለግ እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.