Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪዶር ባለስልጣን ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪዶር አስተዳደር ባለስልጣን ለማቋቋም እና በኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪዶር የተሳለጠ የድንበር ዘለል ስራዎች እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማድረግ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር ተካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር ሸምሱ ከጅቡቲ የወደቦች እና ነጻ ቀጠናዎች ባለስልጣን ሊቀ መንበር ኦማር ሀዲ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪዶር ባለስልጣን ማቋቋም እንዲሁም ባለስልጣኑ የሚኖሩት ኃላፊነቶች እና ስራዎችን አስመልክቶ ፍሬያማ ምክክር አድርገዋል፡፡
በአቶ አብዱልበር ሸምሱ የተመራ ልዑክ በጅቡቲ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረገ መሆኑን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.