አሜሪካ ለኢትዮጵያ የ112 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የሚውል ተጨማሪ የ112 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርጋለች፡፡
ድጋፉ በአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች የአስቸኳይ ጊዜ የኤች አይ ቪ ኤድስ ማገገሚያ እቅድ ፕሮግራም (ፔፕፋር) በኩል የሚተገበር ሲሆን፥ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2030 ኤች አይ ቪ ኤድስን ለማጥፋት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ የሚውል መሆኑ ታውቋል።
የተደረገው ድጋፍ በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ ዜጎች የሚደረገውን እንክብካቤ ለማጠናከር እና በ2030 ኤች. አይ .ቪ ኤድስን ከህብረተሰብ ጤና ስጋትነት እንዲወጣ ለማድረግ ያግዛል ተብሏል፡፡
አሜሪካ በዚህ ፕሮግራም በኩል ባለፉት 20 አመታት በኢትዮጵያ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል የሚውል 3 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጓን የአሜሪካ ኤምባሲ የላከልን መረጃ ያመላክታል፡፡