Fana: At a Speed of Life!

ራሚስ ባንክ ተመርቆ ስራውን በይፋ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመው ራሚስ ባንክ ተመርቆ ሥራውን በይፋ ጀምሯል፡፡

ባንኩ ከሁለት ቢልየን ብር በላይ ካፒታል እና ከ8 ሺህ በላይ ባላክሲዮኖችን በመያዝ የተመሰረተ ባንክ ነው።

ራሚስ ባንክ በኢትዮጵያ ካሉት ከወለድ ነፃ አገልግሎት ከሚሰጡ ባንኮች መካከል አራተኛ ባንክ ሆኖ ነው አገልግሎቱን በይፋ የጀመረው።

የባንኩ ወደ ስራ መግባት በተለይ በፋይናንስ ኢንዱስትሪው ተደራሽነቱን በማስፋት በሀገሪቱ ተወዳዳሪ ኢኮኖሚን ለመፍጠር ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴን ጨምሮ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣ የብሔራዊ ባንክ ም/ገዥ ሰለሞን ደስታ፣የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የሐይማኖት አባቶች እንዲሁም የባንኩ አመራሮችና ባለአክሲዮኖች ተገኝተዋል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.