ኮቪድ-19ን ለመከላከል በምንሰማቸው በጎ ውጤቶች ሳንዘናጋ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃችችን መቀጠል አለብን- ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ለመከላከል በምንሰማቸው በጎ ውጤቶች ሳንዘናጋ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃችንን መቀጠል አለብን አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፥ “የኮሮና ቫይረስን በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዳይስፋፋ ለመከላከል ለምናካሂደው ጥረት አንዱ ዕንቅፋት መዘናጋት ነው” ብለዋል።
“በበሽታው በጣም የተጎዱት የዓለም ክፍሎች እየተረጋጉ ቢሆኑም የእኛን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ሀገሮች ገና የመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንገኛለን” ሲሉም ገልፀዋል።
ቫይረሱ በተሳካ ሁኔታ በቁጥጥር በዋለበት ቦታ እንኳን እንደገና ራሱን የመቀየር ዐመል ስላለው ለረጅም ጊዜ ከእኛ ጋር እንደሚቆይ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ያስታወቁት።
“ስለዚህ በምንሰማቸው በጎ ውጤቶች አንዘናጋ፤ ሳንዘናጋ እስከ መጨረሻው የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃችንን መቀጠል አለብን” ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision