የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ልዑክ ከቻይና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ የሥራ ሀላፊዎች ጋር ተወያየ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ልዑክ ከቻይና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ የሥራ ሀላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡
ልዑኩ በሁለቱ ሀገራት መካከል በፈረንጆቹ 2022 በተፈረመው እና የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት እና ንግድ አማራጮችን በጋራ ማስተዋወቅን አላማ ባደረገው የመግባቢያ ሰነድ አፈፃፀም ሂደት ላይ መክሯል፡፡
በዚሁ ወቅት ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እና የቻይና ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጀኔራል ሊ ያንግ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
በቻይና ቤጂንግ ጉብኝት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ልዑክ ከቻይና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ የሥራ ሀላፊዎች ጋር መምከሩን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!