“ዘ ዊኬንድ” መጠሪያውን ወደ ትውልድ ሥሙ አቤል ተሥፋዬ መኮንን መለሰ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ዘ ዊኬንድ” መጠሪያውን ወደ እውነተኛ የትውልድ ሥሙ አቤል ተሥፋዬ መኮንን መመለሱን አስታወቀ፡፡
ካናዳዊው አርቲስት ከሰኞ ዕለት ጀምሮ የትዊተር እና የኢንስታግራም አካውንቱን ወደ መደበኛው የትውልድ ሥሙ በመቀየር መጠቀም ጀምሯል።
የአሁኑ ለውጥ “ዘ ዊኬንድ” የሚለውን ማንነት ቀስ በቀስ የመግደል ሰፊ ዕቅድ ጅማሮ እንደሆነ” መግለጹን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡
በአዲስ ማንነት ለመወለድ እና አቤል በሚለው የትውልድ መጠሪያው ቀጣዩን የሙዚቃ አልበም ለአድማጮቹ ለማድረስ ዕቅድ እንዳለውም ገልጿል።
ከዚህ በኋላም በሙዚቃ ኢንዱስትሪ መለያው “ዘ ዊኬንድ” ሳይሆን በትክክለኛው የትውልድ ሥሙ አቤል ተሥፋዬ እንዲጠራ የጥበብ አድናቂዎቹን ጠይቋል፡፡
አያይዞም “ከቀድሞ ማንነቱ በመውጣት እንደገና የመወለድ ፍላጎት እንዳለው ተናግሯል፡፡
አርቲስት አቤል በእናቱ ሥም በ“ሳምራ ቡና” የንግድ ምልክትየሚታወቀውን የኢትዮጵያን ቡናም እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡