Fana: At a Speed of Life!

የቻይናዋ ቾንግቺንግ ግዛት ባለሐብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ-ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የቻይናዋ ቾንግቺንግ ግዛት ባለሐብቶች ኢትዮጵያን መርጠው የንግድ መዳረሻ እንዲያደርጓት ተጠየቁ፡፡

በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቻይና ቾንግቺንግ ማዘጋጃ ቤት የውጭ ጉዳይ ፅኅፈት ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሊ ሚንጉዋን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡

በውይይታቸውም ፥ በቾንግቺንግ ግዛት የሚገኙ ኩባንያዎችም ኢትዮጵያን መርጠው የንግድ መዳረሻ እንዲያደርጓት ሊ ሚንጉዋን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል፡፡

አምባሳደሩ ÷ የኢትዮጵያና የቻይና ወዳጅነትና ትብብር ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ላለችው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ቁልፍ ሚና እንዳለው ነው በውይይታቸው ወቅት የገለጹት፡፡

ቻይና በኢትዮጵያ ዕድገት ውስጥ የተለየና አይተኬ ቦታ እንዳላትም አንስተዋል፡፡

በተለያዩ መሥኮችና የንግድ ልውውጦች በኢትዮጵያ መዋዕለ-ንዋያቸውን ማፍሰስ ለሚፈልጉ የቻይናዋ ቾንግቺንግ ግዛት ባለሐብቶች ጥሪ ማቅረባቸውን በቻይና ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ሊ ሚንግዋን በበኩላቸው ÷ በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለው ሁለንተናዊ ስትራቴጂያዊ ትብብር ኢንቨስትመንትን፣ ንግድንና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.