Fana: At a Speed of Life!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ዜጎችን አያያዝ መጎብኘት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ዜጎችን አያያዝ መጎብኘት ጀመረ።

መርማሪ ቦርድ በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ዜጎችን በዛሬው እለት መጎብኘት መጀመሩን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በምልከታውም መንግስት ለዜጎች የሰጠው ትኩረት እና ዜጎች ያሉበት አጠቃላይ ሁኔታ እንዲሁም ከሰብዓዊ መብት አንጻር ምልከታ እንደሚደረግ መርማሪ ቦርዱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መግለፃቸው ይታወሳል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለመቆጣጠርም ቦርዱ ክትትል እያደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመቆጣጠር መንግስት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም የሚከታተል መርማሪ ቦርድ መቋቋሙ ይታወቃል።

ቦርዱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ወቅት የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ተከታትሎ በህግ ፊት ማቅረብ፥ በዚህ ምክንያት ወደ ማረሚያ የሚገቡ ካሉም ከታሰሩበት ተገቢነት አንጻር በመመልከት የምርመራ ውጤቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማቅረብ ሃላፊነት አለበት።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.