Fana: At a Speed of Life!

1 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው – የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለፀ፡፡

በዚህም በግለሰብና በተቋማት በተያዙ 80 ሺህ ችግኝ ጣቢያዎች ችግኝ የማፍላት ስራው እየተሰራ መሆኑንም ቢሮው ገልጿል፡፡

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አልማዝ ጊዜው (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት ÷እስካሁን 1ነጥብ 1ቢሊየን ችግኝ ማፍላት ተችሏል፡፡

201 ሺህ ሄክታር መሬት ለተከላው የተዘጋጀ ሲሆን÷ ጉድጓድ የማዘጋጀትና ግብረሃይል የማዋቀር ስራ እየተሰራ ነውም ብለዋል።

በሳምራዊት የስጋት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.