የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፓኪስታን ካራቺ የቀጥታ በረራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት አራት ጊዜ ወደ ፓኪስታን ካራቺ የሚያደርገውን በረራ በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።
አየር መንገዱ ወደ ፓኪስታን ካራቺ የሚያደርገው የቀጥታ በረራ የሁለቱን ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እንደሚያጠናክር ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር በማሳደግ የሀገራቱን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡
የቀጥታ በረራው አየር መንገዱ ወደ እስያ ሀገራት የሚያደርገውን የበረራ ቁጥር ወደ 37 ከፍ እንደሚያደርገው ተጠቁሟል፡፡
በቅድስት ብርሃኑ