Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምስጋኑ አርጋ ከአንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምስጋኑ አርጋ ከአንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ።

ሚኒስትር ዴኤታው “በውይይታችን ዋና ፀሀፊውም ሆኑ ተመድ ለኢትዮጵያ እያደረጉት ላለው ድጋፍ ያለንን አድናቆት ገልጬላቸዋለሁ” ብለዋል።

በድህረ ጦርነት ወቅት የሚከናወኑ የመልሶ ግንባታ ስራዎች በማገዙም ረገድ በኢትዮጵያ እና በተመድ መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ከስምምነት መደረሱንም ነው ያመለከቱት።

አምባሳደር ምስጋኑ፥ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ስለሚገኝበት ደረጃም ገለፃ አድርገውላቸዋል።

አንቶኒዮ ጉተሬዝ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ የሰሜኑን ግጭት ፈታ በፍጥነት ለውጥ እያሳየች በመሆኑ መደሰታቸውን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በቀጣናው ቁልፍ ሚና የምትጫወት ሀገር እንደመሆኗም፥ በሀገሪቱ ያለው ሰላምና መረጋጋት ለአካባቢው አወንታዊ ትርጉም አለው ብለዋል።

የተገኘውን ሰላም ለማፅናት ሀገሪቱ የምታደርውን ጥረት ተመድ እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.