Fana: At a Speed of Life!

በ100 ሚሊየን ብር በጅግጅጋ እየተገነባ ያለው የዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ከ1 ወር በኋላ ይጠናቀቃል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ100 ሚሊየን ብር ወጪ በጅግጅጋ ከተማ በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት እየተገነባ ያለው የዱቄት እና የዳቦ ፋብሪካ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ።

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን የዱቄት እና የዳቦ ፋብሪካውን ግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል፡፡

ፋብሪካው እየተገነባ የሚገኘው በጅግጅጋ ከተማ በ 10 ሺህ ሔክታር ላይ ነው፡፡

ፋብሪካው ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በቀን 420 ኩንታል የስንዴ ዱቄት እና 300 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም አለው መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ፋብሪካው በጅግጅጋና አካባቢው ለሚገኙ የስንዴ አምራች አርሶ አደሮች የገበያ ትስስር እንደሚፈጥር ተመልክቷል፡፡

በተጨማሪም በአነስተኛ ዋጋ የዳቦ አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል ያግዛል ሲሉ አቶ ኢብራሂም ተናግረዋል።

ለግንባታው መጠናቀቅ የክልሉ መንግሥት ድጋፍ እንደሚደርግም አረጋግጠዋል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ከዚህ በፊት ዘመናዊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስገንባቱ ይታወሳል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ የዱቄት እና የዳቦ ፋብሪካ ለመገንባት ከመረጣቸው 10 ከተሞች ውስጥ ጅግጅጋ አንዷናት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.