Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለተለያዩ አካባቢ ወጣቶች የበዓል ስጦታ አበረከቱ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለተለያዩ አካባቢ ወጣቶች የበዓል ስጦታ አበረከቱ።

ለተለያዩ አካባቢዎች 40 በሬዎች የተከፋፈሉ ሲሆን ስጦታዎቹ ከባለሀብቶች የተሰባሰቡ ናቸው።

ወጣቶቹም ስጦታውን በመቀበል ለየአካባቢው አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የሚያከፋፍሉ ይሆናል።

ከኢትዮ አግሪ ሴፍት የተበረከተው ስጦታ በመዲናዋ ለተለዩ 40 ሰፈሮች የተሰጠ ሲሆን በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አማካኝነት በቅርጫ ተከፋፍሎ ለአቅመ ደካማ ቤተሰቦች እንዲደርሳቸው ይደረጋል ተብሏል።

ኢንጂነር ታከለ በከተማዋ በተለያየ አካባቢ ለሚገኙ ወጣቶች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ወጣቶቹ ለከተማ አስተዳደሩ ጥሪ የሰጡትን ፈጣን ምላሽም አድንቀዋል።

በየአካባቢዎቹ የሚገኙ አቅመ ደካማዎችን በመደገፍ ወጣቶቹ እያሳዩ ያሉት ተነሳሽነት አርአያ የሚሆን ነው ብለዋል።

ምክትል ከንቲባው በሳምንቱ ከተለያዩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመሆን ለነዋሪዎች የበዓል ስጦታ ማበርከታቸው የሚታወስ ነው።

በትዝታ ደሳለኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.