ብልጽግና ቃል የገባውን በተግባር ማረጋገጥና ፈተናዎችን ወደ እድል መቀየር መለያው መሆኑን እያረጋገጠ ይገኛል – አቶ አደም ፋራህ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልጽግና ፓርቲ ቃል የገባውን በተግባር ማረጋገጥና ፈተናዎችን ወደ እድል መቀየር መለያው መሆኑን በቀጣይነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለፁ።
አቶ አደም፥ ብልጽግና ፓርቲ ካለፈው ምርጫ በኋላ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸው፥ ፓርቲው በጉባኤው በኢኮኖሚ ዘርፍ ካስቀመጣቸው ግቦች መካከል በ10 አመት ውስጥ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 5 ጠንካራ ኢኮኖሚ ባለቤት ሀገራት መካከል አንዷ እንድትሆን ማድረግ እንደሚገኝበት አስታውሰዋል።
ይሁንና ገና ሁለት አመት ሳይሞላ ፓርቲው ግቡን ማሳካቱን በማንሳት ከዚህ ቀደም ስንዴን እክስፖርት የማድረግ ግብ በማስቀመጣ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
“በጋራ ጥረት ያስመዘገብነው አመርቂ ውጤት ነውና እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን” ብለዋል በመልዕክታቸው።
ብልጽግና ፓርቲ ቃል የገባውን በተግባር ማረጋገጥና ፈተናዎችን ወደ እድል መቀየር መለያው መሆኑን በቀጣይነት እያረጋገጠ ይገኛልም ነው ያሉት።
“ኢኮኖሚውን ይበልጥ ለማጠናከር፣ ሎሎች የጉባኤያችንን አቅጣጫዎች በውጤታማነት ለመፈፀምና በ10 አመቱ እቅዳችን ያስቀመጥናቸውን ግቦች ለማሳካት ጠንክረን እየሰራን መሆኑን፣ በቀጣይም አጠናክረን እንደምንቀጥል በተለያዩ ማሳያዎች ለሕዝቡ ማረጋገጥ ይኖርብናል” ነው ያሉት።