Fana: At a Speed of Life!

ከ47 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የኮትሮባንድ ዕቃ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን 47 ሚሊየን 537 ሺህ ብር ዋጋ ያላቸው በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ ዕቃዎች ተያዙ፡፡

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ እንደገለጹት÷ መነሻውን ከጅቡቲ አድርጎ በኮንቴነር ታሽጎ ወደ መሀል ሀገር ሊገባ የነበረ ሕገ ወጥ የኮትሮባንድ ዕቃ ትናንት ተይዟል፡፡

መድኃኒት እና ልባሽ ጨርቆችን ጭኖ በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ በሐረማያ ወረዳ ደንገጎ አካባቢ በመገልበጡ በተደረገ ፍተሻ በሕገ ወጥ ሰነድ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

አሽከርካሪው ለጊዜው ከአካባቢው በመሰወሩ ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑን ለፋና ብሮድስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.