በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በጅማ ዞን ጉብኝት አደረገ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በጅማ ዞን የግብርና ልማት ሥራዎችን ጎበኘ፡፡
ልዑኩ በጉብኝቱ÷ በስንዴ፣ ሙዝ፣ የሻይ ቅጠል፣ አቮካዶ እና የተፈጥሮ ማዳበሪያ ልማት ላይ የተጀመሩ ስራዎችን ተመልክቷል፡፡
በጉብኝቱ ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በተጨማሪ የዞን አስተዳደሮች እና የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ከንቲባዎች መገኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡