ከ18 ሺህ የትምህርት ማስረጃዎች 900ዎቹ ሐሰተኛ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18 ሺህ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ የሕጋዊነት ማረጋገጫ ተደርጎ 900ዎቹ ሐሰተኛ ሆነው መገኘታቸውን የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን አስታወቀ።
የትምህርት ማስረጃዎቹ ተመሳስለው የተሰሩ፣ እውቅና ከሌለው ተቋም የተሰጡ፣ ባልተፈቀደ የሙያ መስክ የሰለጠኑ፣ የመቁረጫ ነጥብና የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው የሠለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የማረጋገጥ ስራው የተከናወነው በበጀት ዓመቱ የትምህርት ማስረጃ ሕጋዊነትና ትክክለኝነት እንዲረጋገጥላቸው በጠየቁ 18 ሺህ ደንበኞች መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ባለስልጣኑ በተቀናጀ ከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ፣ የፈቃድ እድሳት፣ ክትትልና ቁጥጥር ላይ በትብብር ለመስራት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ጉዳይ እየተባባሰ መሆኑን ጠቁመው÷ የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ አግባብነት እና ትክክለኛነትን ለማረጋገጥ የጋራ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!