የግብርና ሚኒስቴር ለሶማሌ ክልል160 ነጥብ 1ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል 160 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ ( ዶ/ር) ለሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ አስረክበዋል፡፡
የተደረገው ድጋፍ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ እና ጎርፍ አደጋ ሳቢያ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚውል መሆኑን አቶ ሙስጠፌ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ለምርጥ ዘርና ለማዳበሪያ እንዲሁም ለእንስሳት መኖና መድሃኒት መግዣ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።
አቶ ሙስጠፌ÷ ሚኒስቴሩ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡