ጠ/ሚ ዐቢይ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ወቅትም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መግታትና መቆጣጠር በሚቻልበት አግባብ ላይ መምከራቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።
በዚህ ወቅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ በቫይረሱ ሳቢያ እየተዳከመ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከሰሃራ በታች የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ፈታኝ መሆኑን ሃሳብ ተለዋውጠዋል።
ከዚህ አንጻርም ቫይረሱ የሚያስከትለውን የከፋ ጉዳት መቀነስ የሚያስችል የጋራ አመራር መተግበር በሚቻልበት አግባብ ላይም ውይይት አድርገዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision