Fana: At a Speed of Life!

በጅግጅጋ ከተማ የመጀመሪያው የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል ግንባታ ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅግጅጋ ከተማ የመጀመሪያው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ግንባታ ስራ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
 
በግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የሶማሌ ክልል አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች÷”በአዲስ አበባ ድሃውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እያደረገ ያለውን ስኬታማ ሰው ተኮር ተግባራችን በእህት ከተማችንና የምስራቋ ጮራ ጅግጅጋ ከተማ የመጀመሪያውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ግንባታ ስራ ዛሬ አሰጀምረናል” ብለዋል።
 
የብልፅግናችን ማህበራዊ ፍትህ ፕሮግራም በተጨባጭ ህዝባችንን እየጠቀመ የነበረውን ትስስራችንን እያጠናከረ ነው ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
 
የምገባ ማዕከሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ትብብር የሚገነባ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.