Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስቴር በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ394 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴር ከልማት አጋር አካላት በመሆን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ394 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ድጋፉ ለኦሮሚያ፣ ለሶማሌ እና ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በድርቅ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች እንደሚውል ተጠቅሷል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዴዔታ ፍቅሩ ረጋሳ ድጋፉን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ÷ ለሶስት አመታት በድርቅ የተጎዱ አርብቶ አደር አካባቢዎችን በመከታተል የገንዘብም ሆነ የአይነት ድጋፍ ሲደረግ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

በኦሮሚያ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እና በሶማሌ ክልል በድርቅ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች በዓለም ባንክና በአውሮፓ ህብረት በሚደገፉ ፕሮጀክቶች አማካኝነት ከ394 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

የተቋቋመው የባለሙያዎች ቡድን ድርቁ የተከሰተባቸውን አካባቢዎች በመከታተል ያቀረበውን ሪፖርት መሰረት በማድረግ ብሩ ለእንስሳት መኖ፣ ለመድሐኒትና ለእንስሳት መኖ ዘር ግዢ እንደሚውል መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.