ጀርመን የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ስራዎች እንዲሳኩ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በኢትዮጵያ ከጀርመን አምባሳደር ስቴፍን ኡር ጋር ተወያዩ ።
አምባሳደር ተሾመ÷ የተሃድሶ ኮሚሽን የተቋቋመበትን ዓላማ፣ እስከ አሁን የተከናወኑ የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች እና ከልማት አጋሮች ጋር በጋራ ስለሚሰሩ የአጋርነትና ትብብር ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገዋል።
አምባሳደር ስቴፍን በበኩላቸው÷ ጀርመን በኢትዮጵያ በተለይም በቴክኒክና ሙያ እንዲሁም በግብርና ስራዎች ዋነኛ አጋር መሆኗን አንስተዋል።
የተሃድሶ ኮሚሽን ስራዎች እንዲሳኩ እና ሁለንተናዊ ሰላም እንዲሰፍን ጀርመን የበኩሏን ድጋፍ እንደምታደርግ አምባሳደሩ ቃል መገባታቸውንም የሰላም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡