Fana: At a Speed of Life!

አንቶኒ ብሊንከን አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ  ማምሻውን አዲስ አበባ ገቡ።

ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ  አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

አንቶኒ ብሊንከን  ኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሠላም ለማሥፈን በተወሰዱ እርምጃዎች እና የጦርነት ማቆም ስምምነቱን ተከትሎ አፈፃፀሙ ላይ እንደሚመክሩም ነው የሚጠበቀው።

በተጨማሪም የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት አጋሮችን እና የሲቪል ማኅበረሰብ አካላትንም በማነጋገር የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ፣ በምግብ ዋስትና እና በሰብዓዊ መብቶች ላይም ይወያያሉ ነው የተባለው።

በተጨማሪም ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አንቶኒ ብሊንከን ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በኒጀር የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

በበረከት ተካልኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.