Fana: At a Speed of Life!

ሕገ-ወጥ ንግድ እና ኮንትሮባንድ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በብቃት ለመሰብሰብ ማነቆዎች መሆናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ሕገ-ወጥ ንግድ እና ኮንትሮባንድ እንዲሁም ዘመኑን ያልዋጀ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለአገልግሎት አሰጣጥም ሆነ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በብቃት ለመሰብሰብ ዋነኛ ማነቆዎች መሆናቸው ተገለጸ፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን እና የገንዘብ ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮች በ2015 ቀሪ ወራት በሚሰሩ ስራዎች እና በቀጣይ በጀት ዓመት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱ የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፣ የሶስቱም ተቋማት ሚኒስትር ዴኤታዎች እና ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡

ለውይይት መነሻ በቀረበው ሰነድ እንደተገለጸው የገቢዎች ሚኒስትር እና የጉምሩክ ኮሚሽን በተያዘው የበጀት ዓመት በገቢ አሰባሰብ እና በአገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ አፈጻጸም ማሳየታቸው ተጠቅሷል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የገቢ ሴክተሩ በሙሉ አቅሙ እንዲሰራ እና የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ለማስቻል መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚደርግ አስረድተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.