Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቦረና ዞን የድርቅ ተጎጂዎችያደረገውን ከ250 ሚሊየን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብና የአይነት ድጋፍ አስረከበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቦረና ዞን የድርቅ ተጎጂዎችያደረገውን ከ250 ሚሊየን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብና የአይነት ድጋፍ አስረከበ።
ድጋፉ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ተቋማት እና ክፍለ ከተሞች የተሰበሰበ ነው።
የተሰበሰበው 104 ሚሊየን ብር በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ቢሮዎች፣ ከክፍለ ከተማ እና ወረዳዎች 37 ሚሊየን ብር፣ በከተማዋ ከሚገኙ ባለሀብቶች ደግሞ 109 ሚሊየን ብር በድምሩ ከ250 ሚሊየን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ እና በአይነት ነው።
ድጋፉ የውሃ ቦቴዎች እና የእንስሳት መኖን ያካተተ ነው።
የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ ቦረና የሚታወቀው በደግነት እና በለጋስነት ቢሆንም ረዘም ላለ ጊዜ በድርቅ መጎዳቱን አንስተዋል።
በመሆኑም በዞኑ የሚገኙ ወገኖችን መርዳት የክልሉ መንግስት ብቻ ሀላፊነት ባለመሆኑ ለወገኖቻችሁ እኛም ከጎናችሁ ነን ለማለት ነው ድጋፉን ያደረግነው ብለዋል።
ከንቲባዋ ድጋፉን ለለገሱ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ፥ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ድርቁ የተከሰተው በክልሉ 10 ዞኖች ለተከታታይ 3 አመታት ዝናብ ባለመዝነቡ የተፈጠረ መሆኑን አንስተዋል።
ድርቅን ለፖለቲካ መሳሪያ ለመጠቀም የሚጥሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
የክልሉ መንግስት ለዞኑ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በማንሳት ሁሉም ህብረተሰብ ለዞኑ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።
በፍቅርተ ከበደ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.