ኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና በአፍሪካ ጉዳዮች የቻይና ልዩ መልዕክተኛ ሊዩ ዩሺ በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፡፡
ውይይቱ የተካሔደው ከአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን ነው፡፡
የሥራ ኃላፊዎቹ በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል የቆየውን የረጅም ጊዜ ወዳጅነት አንስተው መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይም የሀገራቱን ግንኙነት በተለያዩ መስኮች ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!