የዓለም ባንክ መንግስት ለሚያከናውናቸው የልማት ተግባራት የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ ከዓለም ባንክ ልዑካን ቡድን አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ተግባራትን በመለየት በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
ሚኒስትሯ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን ልማት በማገዝና በመደገፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አንስተዋል፡፡
ይህ ትብብር እና ድጋፍም በጋራ የልማት ስራዎችን በመተግበር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን በበኩላቸው÷ ባንኩ የኢትዮጵያን እድገት ለማፋጠን መንግስት የሚያከናውናቸውን የልማት ተግባራት በመደገፍ ሲያከናውናቸው የነበሩ ተግባራትን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡