Fana: At a Speed of Life!

አምራች ኢንተርፕራይዞች በተኪ ምርቶች እንዲሰማሩ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች በተኪ ምርቶች ላይ እንዲሰማሩ የሚያስችል የ10 ዓመት ዕቅድ ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታውቋል፡፡

ፍኖተ ካርታው ከጀርመን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ጂ አይ ዜድ) ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑን  የኢንተርፕራይዙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ ተናግረዋል፡፡

ፍኖተ ካርታው አምራች ኢንተርፕራይዞች በውጭ ምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ እደሚያመርቱ የሚያስችል መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ እንዲሆኑ እና ኤክስፖርት ላይ በስፋት እንዲሰማሩ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫዎት ተመላክቷል፡፡

በፍኖተ ካርታው የአምራች ኢንተርፕራይዞች ከፍተኛ ችግር የሆነው የማምረቻ እና መሸጫ ቦታ ችግርን ለመቅረፍ በሌሎች ተቋማት ይሰራ የነበረው በቀጣይ በኢንተርፕራይዙ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

እቅዱ ኢትዮጵያ በዘርፉ አሁን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት በቀጣይ መተግበር ያለባቸውን አቅጣጫዎች እንደሚያስቀምጥም ነው የገለጹት፡፡

ለፍኖተ ካርታው ስኬታማነት ከሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊው ግብዓት መሰብሰቡን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

 

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.