የአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ መሆኑን የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አስታውቋል፡፡
ኢንተርፕራይዙ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ትላንት ሰኞ ምሽት 4:45 ላይ ወደ አዳማ አረቄ ጭኖ እየተጓዘ ክፍያ በር ላይ በተገለበጠ ተሽከርካሪ ምክንያት ባጋጠመ የእሳት አደጋ በህይወትና ንብረትላይ ጉዳት ደርሷል፡፡
ይህን ተከትሎም የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ስለሆነም ደንበኞች በሞጆ 52 ኪሎ ሜትር፣ 56 ኪሎ ሜትር እንዲሁም በ60 ኪሎ ሜትር አማራጭ የጉዞ መስመሮችን እንዲጠቀሙ ኢንተርፕራይዙ አሳስቧል፡፡