አምባሳደር ምሥጋኑ አረጋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አምባሳደር ምሥጋኑ አረጋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አድርገው ሾሙ፡፡
አምባሳደር ምሥጋኑ አረጋ ከጥር 02 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አምባሳደር ምሥጋኑ አረጋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እስከ ተሾሙበት ጊዜ ድረስ የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተመላክቷል።
አምባሳደር ምሥጋኑ ከአሁን በፊት በኳታር እና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ማገልገላቸውን የሚታወስ ነው፡