Fana: At a Speed of Life!

ዘመናዊ የሴቶች የተሃድሶና ክኅሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘመናዊ የሴቶች የተሃድሶ እና የክኅሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ፕሮጀክት ግንባታ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

የፕሮጀክቱ ውል የመፈራረምና ግንባታ የማስጀመሪያ መርሐ-ግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።

በ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የሚገነባው ፕሮጀክቱ ÷ ማኅበራዊ ጉዳት የደረሰባቸው ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ፣በክኅሎት ለማዳበርና መልሶ ለማቋቋም ያለመ ነው መባሉን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፕሮጀክቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ በማስጀመሪያ መርሐ -ግብሩ ላይ ተመላክቷል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.