ዕሴት የተጨመረበት የውጭ ንግድ ደረጃ ያለውን ቡና በሀገር ውስጥ በውጭ ምንዛሬ ለመሸጥ የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ ወጣ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዕሴት የተጨመረበት የውጭ ንግድ ደረጃ ያለውን ቡና በሀገር ውስጥ በውጭ ምንዛሬ ለመሸጥ የሚያስችል ረቂቅ የአፈጻጸም መመሪያ አወጣ፡፡
ረቂቅ መመሪያው ለተጨማሪ ግብዓት ይፋ የተደረገው በቡና ግብይትና ጥራት ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1051/2009 አንቀጽ 24 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት በተሠጠው ሥልጣን መሆኑንም ከገጹ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ረቂቅ መመሪያውን ከዛሬ ጀምሮ እስከ 15 ቀናት ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተመልክተውት አስተያየት እንዲሰጡበት መጠየቁን የባለሥልጣኑ መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-