Fana: At a Speed of Life!

ለገና እና ጥምቀት በዓላት ገበያው ላይ በቂ ግብዓት ይኖራል – የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ለገናና ጥምቀት በዓላት 60 ሺህ ዶሮ ፣ 90 ሺህ ኩንታል ጤፍ እና ከ15 ሺህ በላይ የእርድ እንስሳት ወደ ገበያ እንደሚቀርብ አስታወቀ፡፡

በተጨማሪም በሸማቾች በኩል 5 ነጥብ 4 ሚሊየን ሊትር ዘይትና 30 ሺህ ኩንታል ስኳር ለማኅበረሰቡ ተደራሽ እንደሚሆን ንግድ ቢሮው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ጠቁሟል።

የዋጋ ጭማሪና የምርት መደበቅን ለመከታተልም ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደሥራ መግባቱን የቢሮው ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ ተናግረዋል ።

ይህንን ለመከታተልና ግልፅ ለማድረግም የመረጃ ተደራሽነት ላይ እንዲሰራ ቁጥጥሩን ለማጠናከር በምክትል ከንቲባው የሚመራ የአቅርቦት ንዑስ ኮሚቴ ተቋቁሟልም ነው የተባለው።

ምርት ከክልሎች ወደ ገበያ ማዕከላት በሙሉ አቅም እንዲገባ ዝግጅት መደረጉም ተመላክቷል።

በዚህ ላይም በገበያ ላይ ጫና እንዳይፈጠር ጊዜያዊ የገበያ ማዕከላት ጭምር መቋቋማቸው ነው የተገለጸው።

በአሸናፊ ሽብሩ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.